የደብረ ክዋክብት የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፅዋ ማህበር

መግቢያ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቸርነት ተጠብቃ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበራትን ትውፊቶች ሳይበረዝና ሳይከለስ እስከ ዛሬ ድረስ አቆይታለች፡፡ ከተረከበቻቸው ትውፊታዊ ሥርዓቶች አንዱ የጽዋ ማኅበር ነው። ይህም ሥርዓት ምእመናን በወር ተራ ገብተው እየደገሱ አብረው የሚጸልዩበትና ለችግረኞችም የሚረዱበት የክርስትና ምልክት ከመሆኑ በላይ ክርስትናውም እንደሚጠፋ ጠንቅቀው የሚያውቁት የቀደሙት አባቶቻችን ይህንን በክርስትና ምልክት እንዳይጠፋ ጸንተው ጠብቀው የተረከቡትን አስረክበውናል። የወረሱትን አውርሰነዋል። በመሆኑም አባቶቻችን ያቆዩንን የድንበር ምልክቶች /ሥርዓቶች/ ሁሉ መጠበቅ፤ ጠብቆም ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ ግዴታችን መሆኑን በመረዳት እኛም በከለንና በዱሰልዶርፍ አካባቢ የምንገኝ ምእመናን አማካኝነት የጽዋ ማኅበሩ 2008 ዓ ም ተመሠረተ።
የሚከተለው ዓላማዎች አሉት፦
❖ ፍቅርን ማጠናከር፦ በአባላት መካከል አንድነትንና ክርስቲያናዊ ፍቅርን መመሥረት።
❖ እርስ በርስ መረዳዳት፦ በደስታና በሐዘን (በችግር) ጊዜ መደጋገፍ፡፡
❖ የቤተክርስቲያን ልማት፦ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን መሥራትና ማደስ ንዋያት ቅድሳት የሚጎድላቸውን ገዳማት እና አብነት ት/ቤቶችን መርዳት
❖ መንፈሳዊ ዕድገት፦ በጾም፣ በጸሎትና በንስሐ ሕይወት መበርታት
❖ የቅዱሳንን ታሪክ ማወቅ፦ የማኅበሩን መጠሪያ ቅዱስ ገድልና ታሪክ ማጥናት።


