በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ዱስልዶርፍ ደብረከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፅዋ ማኅበር

መተዳደሪያ ደንብ
የማህበሩ አላማ
2.1 ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ፀጋ በረከትእንድናገኝ በአንድነት በመሆን ፀበል ፀዲቅ ማቅረብ
2.2 የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንንለመጠበቅ፣ለማጠንከር፣ለእድገትዋም ያልተቆጠበ ጥረትማድረግ
2.3 ብራብ አብልታችሁኛል ብጠማ አጠጥታችሁኛል ብታመምጠይቃችሁኛል ብታረዝ አልብሳችሁኛል ብታሰርአስፈትታችሁኛልየሚለዉን አምላካዊ ቃል ምርኩዝ በማድረግ አቅማችንበፈቀደዉ መጠን ለመፈፀም (አብያተ ክርስቲያንን ለመርዳት)
2.4 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከትዉልድትውልድ ትዉፊትን እንዲሻገር አስፈላጊዉን ማህበራዊአስተዋፅ ማድረግ
2.5 አስራት በኩራት ማዉጣት ሚልኪ3:10 እንደተፃፈዉ በቤቴዉስጥ መብል እንዲሆን አስራቱን ሁሉ ወደ ተራራ አግቡየሰማይ መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከትንም አትረፍርፊባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ የሰራዊት ጌታ እግዚያብሄርበሚለዉን አምላካዊ መርህ መሰረት እንዲፈፀም ማትጋት
የአባሉ ኃላፊነት መብት እና ግዴታ
4.1 እያንዳንዱ አባል የማኅበሩን ደንብና መመሪያ አክብሮየማስከበር ኃላፊነቱን መወጣት
4.2 ወር በገባ በ20 የዋዜማ ፀሎት መሳተፍ
4.3 ዝከር (ፅዋ)በሚዘጋጅበት እለት ሁሉም አባል መሳተፍ አለበት
4.4 ዝከር (ፅዋ) ለማዘጋጀት ተረኞች ቤተከርስቲያን (ጓዳችንን) የምንጠቀምበትን ነገር ማየት ይጠበቅብናል። እንደዚሁምፕሮግራሙ ሲያበቃ ሁሉንም ነገር አስተካክለን(አፅድተን)ማስረከብ አለብን
4.5 የተዘጋጁትን ያሬዳዊመዝሙሮች አጥንተን መዘመርአለብን


